June 21, 2018
የአገራችን አንድነትና የትክክለኛ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የታገልንላቸውና ወደፊትም የምንታገልላቸው አገራዊ ራእዮች ናቸው
ለዘመናት በአገራችን የተካሄደው የዲሞክራሲ የፍትህና የእኩልነት ትግል በየጊዜው በአውቃለሁ ባዮችና በጉልበተኞች እየተጠለፈ በቀረብነው ቁጥር እየራቀን እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የንብረት ዋጋ ሲያስከፍለን ቆይቷል።
ይህ በየጊዜው የደረሰብን የቅልበሳ ሴራ ካደረሰበን የህይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ባሻገር በማህበራዊ ትስስራችንና በአገራዊ አንድነታችን ላይ የጋረጠው አደጋም በቀላሉ የሚገመት አይደለም። በተለይም ባለፉት ሶስት አስርተ አመታት ውስጥ ዲሞክራሲን በስም ብቻ አንግቶ ከሰልጣን መንበር ላይ ቁጢጥ ያለው የሕወሓት/ ኢሕአዴግ መንግስት የዲሞክራሲ ተሰፋን በመላው አገሪቱ ለማጨለምና ብሎም ለማጥፋት በፖለቲካው በኢኮኖሚውና ማህበራዊ ዘርፍ የሸረባቸው እኩይ ሴራዎች ለዘመናት ተዋልደውና ተጋብተው የኖሩትን የአገራችን ማህበረሰቦች በጠላትነት እንዲተያዩና ደም እንዲቃቡ በፖሊሲ ደረጃ አቅዶ ተፈጻሚ ለማድረግ ሲሰራበት እንደቆየ የአደባባይ ምስጢር ነው።
ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ