Category Archives: Uncategorized

Stop systmatic eviction of Afar pastoralists by Somali Region Special Militia

Posted on by 0 comment

ከአፋር ህዝብ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የአፋር ህዝብ ፓርቲ (አህፓ) ሀገራዊውን የፖለቲካ ምህዳር መስፋትን ተከትሎ ወደ ሀገር ከተመለሰ እነሆ ሁለት ዓመት አስቆጥሯል። ፓርቲያችን ወደ ሃገር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኮች ሃገራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል። የአፋር ህዝብ ፓርቲ በሃገራችን የተጀመረውን ረፎርም በአጭር ጊዜ ዉስጥ ያስመዘገባቸው የለውጥ ሂደቶችን ይደግፋል ያበረታታልም። ይሁንና በዚህ የለውጥ ሂደት ዉስጥ ወክለነዋል የምንለው የአፋር ህዝብ እንደ ህዝብ በሰላም የመኖር ዋስትና ፤ እንዲሁም እንደ ክልል ለመቀጠል የተደቀነበት ስጋት መቀረፍ አለመቻሉ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ለዚህ ስጋት ምንጭ የሆነው በአፋር አርብቶ አደሮችና በሶማሌ ክልል መካከል ለዘመናት መፍትሄ ያላገኘው ጦርነት በዋናናት ሊጠቀስ ይችላል። ይህ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውና በሶማሌ ክልላዊ መንግስት አዝማችነት እየተካሄደ ያለዉን የግዛት ማስፋፋት ጦርነት ከፌዴራል መንግስት እልባት አለማግኘቱ መላውን የአፋር ህዝብ ቁጭትና ቁጣ ዉስጥ አስገብቶታል።

ፓርቲያችን ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የፌደራል መንግስት ህገ-መንግስቱን ማዕከል ያደርገ መፍትሄ መሰጠት አለበት በማለት ላለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ መንግስትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሲያስታዉቅ ቆይቷል። ይሁንና የፌዴራል መንግስት እልባት ሳያገኝለት ወይም ፍላጎት ሳይኖረው በመቅረቱ የንጹሃን ዜጎቻችን ህይወት በየቀኑ እየተቀጠፈ ይገኛናል። ፓርቲያችንም ለህግ የበልይነትና ለዘላቂ ሰላም ቅድሚያ በመስጠት በሶማሌ ልዩ ሃይልና ከባድ መሳሪያ በታጠቁ የተቀናጁ ሐይሎች ህዝባችን እንደቅጠል ሲረግፍና ሲታመስ እያየን መንግስት መፍትሄ ያመጣል በሚል ተስፋ እስካሁ ታግሰናል።

የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ 25/08/2011 ህገመንግስትንና የፌደራል ሰራዓቱን በተጻረር አካሄድ በአፋር ክልላዊ መንግስት ላይ ያወጣውን የጦርነት አዋጅ ተከትሎ ጥቅምት 1/2012 ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ በአፈምቦ ወረዳ ኦብኖ መንደር ባካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ ህጻናትና አዛዉንቶችን ጨምሮ የበርካታ ንጹሃት ህይወት ማለፉ ይታወቃል። የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጦርነት ካወጀ ጀምሮ የአፋር አርብቶ አደር ሳይገደል የዋለበት ጊዜ የለም። ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2012 ተመሳሳይ የተቀናጀና በከባድ መሳሪያ የታጀበ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል በአሚባራና በሃንሩካ ወረዳዎች በፈጸመው ጥቃት የበርካታ ንጹኃን ዜጎች ህይወት አልፎ ብዙዎችም ቆስለዋል።

ይህ ጥቃትና ማፈናቀል እየተካሄደ ያለው በአፋርና በሶማሌ ክልል ድንበር ሳይሆን የአፋር ክልላዊ መንግስት ወሰንን 250 ኪሎሜትር በላይ ዘልቆ በመግበባት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በአካባቢው የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊቱም የአዲስ አበባ-ጂቡቲ መንገድ ደህንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር ለህዝብ ደህንነት ግድ እንደለልው በተግባር አሳይተዋል። ስለሆነም ይህ በአፋር አርብቶ አደር ላይ በተደጋጋሚ እየተደረገ ያለውን ኢ-ሰበዓዊ፤ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ህገመንስታዊ የመሬት ወራራ እና ግድያን በመቃወም የአፋር ህዝብ ፓርቲ የሚክተለውን ባለ (5) አምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፤

  1. ከዚህ በፊት በፈደራል መንግስት ተጠንቶ ተግባራዊ ያልሆነው የሁለቱ ክልሎች የወሰን ማካለል ሰራ በስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን እንጠይቃለን፤
  2. የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት እና የመከላከያ ሰራዊት የህዝባችንን ደህንነት እንዲያስከብሩ በተደጋጋሚ ጥሪ ያደረግን ቢሆንም ይህ ሳይሳካ ቀርተዋል፤ በመሆኑም የክልሉ መንግስት የህዝባችንን ሰላም እና ደህንነት እንዲያስጠብቅ የተሰጠውን ህገ-መንግስታዊ ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በጽኑ እናሳስባለን።
  3. የአፋርና የሶማሌ ክልላዊ መንግስታት ግጭቱ ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ እልባት እንዲያገኝና ለዕርቀሰላም አብረው እንዲሰሩ የፌደራል መንግስት ጫና እንዲያሳድር እንጠይቃለን።
  4. የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጀው ጦርነት ህይወታቸው ላለፈ፣ለተፈናቀሉና ለቆሰሉ የአፋር አርብቶ አደሮች ተገቢውን ካሳ እንዲክፍልና በዚህ ወንጀል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ አለበት።
  5. በሌላ በኩል በዚህ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው የፖለቲካ ሃይሎች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡና ለጋራ ሰላም መስፈን እንዲሁም አብሮ መኖርን ያስቀደመ ፖለቲካዊ መርህ እንዲከተሉ እናሳስበለን።

 

ግንቦት 3 2012

ሰመራ ኢትዮጵያ

 

 

 

 

 

 

 

APP Press release

 

Category: Uncategorized

Qafar Ummattah Partik wakti caalat wagsisak tece maybalalaqa

Posted on by 0 comment

April_2019 statement Qafaraf

ከአፋር ሕዝብ ፓርቲ ወቅታዊ ሁነታዎችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

Posted on by 0 comment

April_2019 statement Amharic